የአፍሪካ ሰላም እና ደህንነት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢትዮጽያ ፌደራል ፖሊስን ጎበኙ

You are currently viewing የአፍሪካ ሰላም እና ደህንነት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢትዮጽያ ፌደራል ፖሊስን ጎበኙ

AMN ህዳር 17/2017 ዓ .ም

በአዲስ አበባ መካሄድ የጀመረዉ በአፍሪካ ሰላም እና ደህንነት ላይ የሚመክረዉ ኮንፈረንስ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል፡፡

የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች በኢትዮጽያ ፌደራል ፖሊስ ተገኝተዉ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

የኢትዮጽያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ የፌደራል ፖሊስ ዘመናዊ አሰራሮችን ከዘመናዊ ቴክኖሎጅ ጋር አቀናጅቶ በመያዝ አስተማማኝ አቅምን ስለመገንባቱ ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ በርካታ ለዉጥና ማሻሻያዎችን በማድረግ አመርቂ ለዉጥን አስመዝግቧል ያሉት ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ የፎረንሲክ ምርመራ እና ምርምር ልህቀት ማዕከል ለዚህ ሁነኛ ማሳያ ነዉ ብለዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይ የሰላም ሚንስትር ብናልፍ አንዷለምን ጨምሮ የአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት ሚኒስትሮች እንድሁም የፀጥታ አካላት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

በተመስገን ይመር

#Addisababa

#Ethiopia

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

https://linktr.ee/AddisMediaNetwork

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review