የአፍሪካ ድምጽ በዓለም መድረኮች እንዲሰማ እና ህብረቱ እንዲጠናከር በተከናወኑ ስራዎች አበረታች ስኬቶች ተመዝግበዋል

You are currently viewing የአፍሪካ ድምጽ በዓለም መድረኮች እንዲሰማ እና ህብረቱ እንዲጠናከር በተከናወኑ ስራዎች አበረታች ስኬቶች ተመዝግበዋል

AMN – የካቲት 5/2017 ዓ.ም

የአፍሪካ ድምጽ በዓለም መድረኮች እንዲሰማ እና ህብረቱ እንዲጠናከር በተከናወኑ ስራዎች አበረታች ስኬቶች መመዝገባቸውን የሞሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶክተር መሀመድ ሳሌም ኦድ ገለጹ።

46ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ “የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ዘርዓ-አፍሪካውያን” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

የሞሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶክተር መሀመድ ሳሌም ኦድ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ አመቱ በርካታ ስኬቶችን እና ብዙ ፈተናዎችን ያመጣ እንደሆነ ገልጸዋል።

የአፍሪካ ድምጽ በዓለም መድረኮች እንዲሰማ ህብረቱ እንዲጠናከር የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።

እንዲሁም በተለያዩ መድረኮች ተሳትፎ በማድረግ በርካታ ስኬት መመዝገቡን ገልጸዋል።

በሰላም እና ጸጥታ፣በምግብ ዋስትና፣ በግብርና እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉን ጠቁመዋል።

የአፍሪካ ህብረትን የሚያጠናክሩ የአህጉሪቱን ህዝብ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች መሰራታቸውን አመላክተዋል።

በልማት በሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም እጅግ ጠቃሚ ተግባራት መከናወናቸውን አመላክተዋል።

ህብረቱን ማጠናከር የምንጊዜም ተቀዳሚ ስራ መሆኑን ገልጸው፥ የአፍሪካ ህብረት ተቋማዊ ማሻሻያ ውጤታማ እንዲሆን አባል ሀገራት ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ያለው ጊዜ አጭር መሆኑን በመገንዘብ በአፋጣኝ ያሉ ክፍተቶችን ማረም እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review