የኢሬቻ በዓል የአብሮነት፣ የአንድነት እና የእርቅ በዓል ነው፦ የኃይማኖት አባቶች

You are currently viewing የኢሬቻ በዓል የአብሮነት፣ የአንድነት እና የእርቅ በዓል ነው፦ የኃይማኖት አባቶች

AMN – መስከረም 23/2017 ዓ.ም

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የኢሬቻ ፌስቲቫል በድምቀት ተካሄዷል።

የኢሬቻ በዓል የአብሮነት በዓል ነው ያሉት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ገመቹ፣ የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ከተለያዩ ቦታዎች ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ እንግዶችን ለመቀበል ክፍለ ከተማው ዝግጅት ማድረጉን ተናግረዋል።

በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የኃይማኖቶ አባቶች የኢሬቻ በዓል የአብሮነት፣የአንድነት እና የእርቅ በዓል መሆኑን በማንሳት ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ሁሉም እንዲሰራ ጠይቀዋል።

በፌስቲቫሉ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተፈራ ሞላ፣ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ገመቹ፣ የክፍለ ከተማው የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ሌማንቾ እና ሌሎች የከተማና የክፍለ ከተማ አመራሮች፣ አባገዳዎች፣ሀደ ስንቄዎች፣ፎሌዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

በመሃመድኑር ዓሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review