የኢትዮ-ብራዚል የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በሳኦ ፖሎ ተካሄደ

You are currently viewing የኢትዮ-ብራዚል የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በሳኦ ፖሎ ተካሄደ

AMN – ሚያዚያ 01/2017

ብራዚል የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት የተዘጋጀው የኢትዮጵያ እና ብራዚል የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በሳኦ ፖሎ ተካሂዷል።

በብራዚል የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ በኢትዮጵያ የተካሄደው ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል በመፍጠሩ የብራዚል ኩባንያዎች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

አምባሳደር ልዑልሰገድ ታሪካዊው የኢትዮ-ብራዚል ግንኙነት ወደ ተጠናከረ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ሊሸጋገር እንደሚገባውም ገልጸዋል።

አምባሳደሩ የብራዚል ኩባንያዎች መንግሥት ትኩረት በሰጣቸው በግብርና፣ በማምረቻው ዘርፍ፣ በታዳሽ ኃይል፣ በማዕድን፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ እንዲሁም በቱሪዝም ዘርፎች ቢሰማሩ የበለጠ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።

በፎረሙ ላይ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ዮሐንስ ፋንታ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና የመንግሥት ፖሊሲ ዙሪያ ሰፊ ገለጻ አቅርበዋል።

በብራዚል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር አንቶኒዮ ሴዛር በበኩላቸው ብራዚል ከኢትዮጵያ ጋር በንግድ እና ኢንቨስትመንት ያላትን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን መግለጻቸዉን ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review