AMN – የካቲት 10/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ መንግስት በኢኮኖሚና ፖለቲካ፤የሴቶችን ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ለማሻሻል ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ሲሉ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ገለጹ፡፡
ቀዳማዊ እመቤቶች የላቀ አመራር በመስጠት፣አፍሪካዊ እሴቶችን በማጎልበት፤ሴቶችን በሁሉም መስክ በመደገፍ ለመሪነት ለማብቃት በትኩረት መስራት እንዳለብን 29ኛው የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች ጠቅላላ ጉባኤ መሪ ቃል ያመላክታል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ መንግስት በኢኮኖሚና ፖለቲካ፤የሴቶችን ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ለማሻሻል ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡
የቀዳማዊ እመቤት ጽ/ቤታችንም እንዲሁ ሴቶችን በኢኮኖሚው ማብቃት ላይ በማተኮር ሶስት (3) ዋና ዋና ሀገር አቀፍ ፕሮጀክቶችን እየተገበረ ይገኛል ማለታቸውን ከጽ/ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡