የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የወታደራዊ ሳይንስና የቴክኖሎጅ መፍለቂያ ማዕከል ነው፦የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት

AMN-ኅዳር 21/ 2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ብዙ ስኬቶችን እያረጋገጠ የሚገኝ የሃገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ የሳይንስና የቴክኖሎጅ መፍለቂያ ማዕከል ነው ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገልፀዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ዩኒቨርሲቲው እየሰራቸው የሚገኙ የትምህርት ፕሮግራሞችን፣ የሳይንስ ተኮር የቴክኖሎጅ የምርምር ውጤቶችን እና የግብርና ፈጠራ የልማት ስራዎችን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል ።

በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኮማንዳንት ብርጋዲየር ጀኔራር ከበደ ረጋሳ አቀባበል እና ሰፊ ገለፃ የተደረገለት የምክር ቤቱ አባላት ዩኒቨርሲቲው ለሃገር ሠላም ህይወቱን የሚሰጥ ፣ፈጠራ የሚሰራ ፣ቴክኖሎጅ የሚመራመር፣ እውቀትና ልምድ ተጠቅሞ ልማት እያለማ የሚገኝ የሃገሪቱ መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ የልህቀት ማዕከል መሆኑን ገልጸዋል ።

የሃገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት አቅም በአለም አቀፍ ደረጃ የተወዳዳሪነት ሚናው ከፍተኛ እንዲሆን በሚያስችል አግባብ ብዙ ችግሮችን አቅፎ እየሰራቸው የሚገኙ ስኬታማ የሳይንስና የቴክኖሎጅ የምርምር ውጤቶች እንደ ሃገር ትልቅ ፋይዳ እንዳለቸው በመገንዘብ ለዩኒቨርሲቲው ትኩረት መስጠትና መደገፍ እንደሚያስፈልግም የምክር ቤቱ አባላት በጉብኝታቸው ወቅት አሥገንዝበዋል።

ዩኒቨርሲቲው ካላው ውስን በጀት ላይ ቀንሶ በስፋት እየሰራቸው የሚገኙ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ስራዎችም የአካባቢውን ማህበረሰብ ችግር በዘላቂነት የሚፈቱና ተጠቃሚ እያደረጉ የሚገኙ ተደራሽ ስራዎችን ጭምር በመስራት የአለኝታነት ሚናውን በተግባር እየተወጣ እንደሆነም በተግባር አረጋግጠዋል ።

ብቸኛው የሃገሪቱ ወታደራዊ የትምህርት ተቋም የመከላከያ ሠራዊቱን ዓለም አቀፋዊ የልህቀት ተወዳዳሪነት በሚመጥን አግባብ እንዲሆን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጀምሮ እስከ ክልል መንግስታት ድረስ ከፍተኛ ትኩረትና ድጋፍ እንደሚያስፈልገውም በምልከታው ላይ ተጠቁሟል ።

ለአገር ክብር እና ለመከላከያ ሠራዊቱ እድገት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመበት የአዋጅ ደንብም እንደገና ለአሰራር በሚያመች አግባብ መልሶ መታየት እንዳለበት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሠላም ጉደዮች ቋሚ ኮሚቴ በጉብኝት ውሎው መገንዘቡን ከመከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review