የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ራሱን በማጠናከር ረገድ ባለፉት ጊዜያት በርካታ ሥራዎች ማከናወኑን የባህር ኃይሉ ዋና አዛዥ ሬር አድሚራል ክንዱ ገዙ ገልጸዋል።
የባህር ኃይል ስራን የተመለከተ ውይይት ተካሂዷል።
የባህር ኃይል ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ካፒቴን እንግዳው ወርቁ፣ የተከናወኑ ስራዎችን አስመልክቶ ገለፃ አድርገዋል።
ካፒቴን እንግዳው የኢትዮጵያ ባህር ኃይል የሰለጠነ የሰው ኃይል ልማት ሥራ፣ አቅም ግንባታ እና መሠረተ ልማት ግንባታዎች ላይ የሠራዊቱን ወታደራዊ ዝግጁነት በማሳደግ እና ራሱን በማጠናከር ረገድ ስኬታማ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ባህር ኃይ ዋና አዛዥ ሬር አድሚራል ክንዱ ገዙ፣ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ባለፉት ጊዜያት በርካታ ሥራዎች ማከናወኑን ገልጸዋል።
ባህር ኃይሉን ማጠናከር እና ሰራዊቱ ተጨማሪ ጠንካራ ኃይል ለመሆን እያከናወነ ያለውን ዘርፈ ብዙ ስራ መደገፍ እንደሚገባ አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ ባህር ኃይል የተጀመሩ ውጤታማ ተግባራትን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና አዛዡ መግለፃቸውን ከሀገር መከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።