AMN – መስከረም 29/2017 ዓ.ም
የ2025 የቻን ውድድር ማጣሪያ ድልድል ከደቂቃዎች በፊት ይፋ ሆኗል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያው ዙር ማጣሪያ ከኤርትራ ብሔራዊ ቡድን ጋር ተደልድሏል።
ብሔራዊ ቡድኑ በደርሶ መልስ ካሸነፈ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ከሱዳን እና ታንዛንያ አሸናፊ ጋር ወደ ዋናው ወድድር ለማለፍ ይጫወታል።
የመጀመሪያው ዙር ማጣሪያ ቀዳሚ ጨዋታ ከጥቅምት 15 እስከ ጥቅምት 17 እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ደግሞ ከጥቅምት 22 እስከ ጥቅምት 24 ይካሄዳሉ።
የሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ቀዳሚ ጨዋታዎች ደግሞ ከታህሳስ 11 እስከ ታህሳስ 13 የመልስ ጨዋታዎች ደግሞ ከታህሳስ 18 እስከ ታህሳስ 20 ይደረጋሉ።
በሀገር ውስጥ ሊጎች ብቻ የሚጫወቱ ተጫዋቾች የሚካፈሉበት ውድድሩ ዘንድሮ በ19 ብሔራዊ ቡድኖችን መካከል እንደሚደረግ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።
የ2025 የቻን ውድድር ከጥር 24/2017 እስከ የካቲት 2/2017 ድረስ በኬንያ ፣ ኡጋንዳ እና ታንዛኒያ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።