የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከግብጽ እና ከጂቡቲ ጋር ለሚኖረው ወሳኝ ጨዋታ በቂ ዝግጅት ማድረጉ ተገለጸ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከግብጽ እና ከጂቡቲ ጋር ለሚኖረው ወሳኝ ጨዋታ በቂ ዝግጅት ማድረጉ ተገለጸ

AMN-መጋቢት 9/2017 ዓ.ም

ቡድኑ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከግብፅ እና ከጂቡቲ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ያደረገውን ዝግጅት አስመልክቶ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ፣ ቡድኑ ለ6 ቀናት በሚያደርገው ውድድር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን ገልጸዋል ።

ቡድኑ በስነልቦናም ሆነ በአካላዊ ብቃት ተገቢውን ዝግጅት ማድረጉን አሰልጣኙ አመልክተው፣ ውድድሮቹን ለማሸነፍ ጥረት እንደሚደረግም አስረድተዋል።

ብሄራዊ ቡድኑ ከየትኛውም ቡድን እኩል መፎካከር የሚያስችለው አቋም ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ወንዶች ብሄራዊ ቡድን አምበል አስቻለው ታመነ ገልጿል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ በአዲስ አበባ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቶ የመጨረሻ 23 ተጨዋቾችን ይዞ ዛሬ ለሊት 6:00 ሰዓት ወደ ሞሮኮ ያመራል፡፡

ዋሊያዎቹ መጋቢት 12 በሞሮኮ ካዛብላንካ በሚገኘው ዛውሊ ስታዲየም ከግብጽ ጋር እንዲሁም መጋቢት 15 ኤል ጀዲዳ በሚገኘው ኤል አብዲ ስታዲየም ከጂቡቲ ጋር የሚያደርገው ወሳኝ ጨዋታ ይጠብቀዋል።

በኦብሲኔት ክፍሌ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review