የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ5 ፓርቲዎችን የማስጠንቀቂያ እግድ ማንሳቱን አስታወቀ

AMN ታህሳስ -2/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. ከጠቅላላ ጉባዔ፣ ከኦዲትና በሴት አባላት ቁጥር አማካኝነት ከሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ጋር በተገናኘ 11 ፓርቲዎች ላይ የዕግድ ውሣኔ ማሳለፉ ይታወቃል።

ቦርዱ ከታገዱት ፓርቲዎች ውስጥ የይቅርታና የመከላከያ መልስ ያቀረቡትን አምስት ፓርቲዎች፤ ማለትም የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎ.ብ.ን)፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ (አ.ት.ፓ)፣ የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋ.ህ.ዴ.ን)፣ የኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ህብረት (ኢ.ዴ.ህ) እና የአገው ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ጉዳይንመመርመሩን አስታውቋል ፡፡

በዚህም ፓርቲዎቹ ያለፈውን ስህተት እንደማይደግሙና በቀጣይም በሚያቀርቧቸው መረጃዎች ጥራት በመተማመን እንዲሁም የቦርዱን ሥራ ከሚያደናቅፍና ዕምነት ጥያቄ ውስጥ ከሚከቱ ተግባራት ተቆጥበው በሕግ አግባብ ብቻ እንደሚንቀሳቀሱ በማመን፤ በማስጠንቀቂያ ዕግዱን ያነሣ መሆኑን ቦርዱ በመረጃው አስታውቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review