የኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማህበር የሴት ነጋዴዎች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ትልቅ ኃላፊነት አለበት-ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

You are currently viewing የኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማህበር የሴት ነጋዴዎች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ትልቅ ኃላፊነት አለበት-ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

AMN-የካቲት 19/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማህበር የሴት ነጋዴዎች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ትልቅ ኃላፊነት አለበት ሲሉ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማህበር የቦርድ አመራሮች ጋር በሴቶች የንግድ እንቅስቃሴ እና ተሳትፎ ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል።

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፣ ማህበሩ ህጋዊ መሰረት በመያዝ የሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደር ተወካዮችን ባካተተ መልኩ፤ በአዲስ መልክ መደራጀቱ መልካም የሚባል እርምጃ መሆኑን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ሴት ነጋዴዎች በሀገር አቀፍ፣ አህጉርና ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ያላቸው ተሳትፎ ማሳደግ እና ጠንካራ ተወዳዳሪ መሆን አለባቸውም ነው ያሉት ሚኒስትሩ።

ማህበሩ ሴት ነጋዴዎች እየተከፈቱ ባሉ አዳዲስ የንግድና ገበያ ዕድሎች ውስጥ በመሳተፍ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለበትም ጠቅሰዋል።

በተለይም በአነስተኛ የንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው እየተጉ ያሉ ሴቶችን በማብቃት የሴቶችን የተሳትፎ መሰረት ማስፋት እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።

የሴቶች ተሳትፎ ለአካታች ኢኮኖሚና ለሀገር ዕድገት ወሳኝ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ በዚህ ረገድም የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለማህበሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review