የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ ሐብት 2.073 ትሪሊዮን ብር ደረሰ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ ሐብት 2.073 ትሪሊዮን ብር ደረሰ

AMN – መጋቢት 25/2017

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ ሐብት 2.073 ትሪሊዮን ብር መድረሱን ባንኩ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ የተቋሙን የስምንት ወራት አፈጻጸም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርበዋል።

አቶ አቤ ሳኖ በሪፖርታቸው እንዳመላከቱት፣ እስከ ፈረንጆቹ በፌብሩዋሪ 2025 መጨረሻ ድረስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ ብር 1.541 ትሪሊዮን፣ ጠቅላላ የብድርና የቦንድ ክምችት መጠን ብር 1.393 ትሪሊዮን፣ እንዲሁም አጠቃላይ ሐብት ብር 2.073 ትሪሊዩን ደርሷል፡፡

ባንኩ በዋና ዋና የአፈፃፀም መለኪያዎች የበጀት ዓመቱ ሲጀመር በኢንዱስትሪው የነበረውን የገበያ ድርሻ ማሳደግ መቻሉም በሪፖርቱ ተገልጿል።

በበጀት ዓመቱ ስምንት ወራት 264 ነጥብ 65 ቢሊዮን ብር ብድር ባንኩ ለደንበኞች ማቅረቡንም አቶ አቤ ሳኖ ጠቅሰው፤ከዚህ ውስጥ 88 ነጥብ 2 በመቶው የተሰጠው ለግሉ ዘርፍ እንደሆነ ነው የተናገሩት።

ባንኩ ብድርን ከማስፋፋት እና የዜጎችን የፋይናንስ ተጠቃሚነት ከማሳደግ አንፃር አዳዲስ የብድር አይነቶችን እያስተዋወቀ እንደሚገኝም አመላክተዋል።

በዲጂታል አማራጭ 717 ሺህ ደንበኞች የብድር አገልግሎት ማግኘት መቻላቸውን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review