የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ አዲስ የቢዝነስ የቻርተር አውሮፕላን ተረከበ

You are currently viewing የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ አዲስ የቢዝነስ የቻርተር አውሮፕላን ተረከበ

AMN – መጋቢት 8/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቦይንግ ኩባንያ የቢዝነስ ቻርተር አውሮፕላን ተረክቧል።

በመረሃ ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ዋና ሃላፊ ለማ ያዴቻ ፣የቦይንግ ኩባንያ ተወካዮችና የአየር መንገዱ የስራ ሀሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው በዚሁ ወቅት፣ ይህ አዲስ አውሮፕላን አየር መንገዱ በአፍሪካ የያዘውን የመሪነት ድርሻ በማሳደግ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን ለማስቀጠል አንድ እርምጃ የሚያሻግረው ነው ብለዋል።

አየር መንገዱ ዛሬ የተረከበው B737-800 የተሰኘ የቻርተር አውሮፕላን ለቢዝነስ ስራዎች፣ለመሪዎች እና ለየት ላሉ አገልግሎት እንደሚውልም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀጣይም የአገልግሎት አድማሱን የማስፋፋት ሂደቱ ተመሳሳይ የቻርተር አውሮፕላኖችን ወደ ገበያው እንደሚያስገባ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አየር መንገዱ ያነገበው የራዕይ 2035 ግቡን ለማሳካትም የላቀ አገልግሎትን ተቀዳሚ ያደረገ ስራ እየሰራ ይገኛል ማለታቸውም ተመላክቷል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review