የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሻርጃ ከተማ ከግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ የበረራ አገልግሎት የሚጀምር መሆኑን አስታውቋል።
አየር መንገዱ በማህበራዊ የትስስር ገጹ ይፋ እንዳደረገው፣ አዲሱ በረራ አገልግሎት በሳምንት ለአራት ቀናት የሚደረግ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚጀምረው አዲስ የበረራ መስመር መንገደኞች በተቀላጠፈ የበረራ አማራጭ የደማቅ ባህልና ሰፊ ኢኮኖሚያዊ እድሎች ባለቤት ወደ ሆነችው ሻርጃ ከተማ በቀላሉ እንዲጓዙ እንደሚያስችልም ገልጿል፡፡