AMN – የካቲት 13/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አመራር አባላት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቪርስቲ፣ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል፣ የኢትዮጵያ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት እና የምስለ በረራ ክፍልን የስራ እንቅስቃሴዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እና ከአየር መንገዱ የአመራር አባላት ጋር በአየር መንገዱ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስር ከሚተዳደሩ የመንግስት የልማት ድርጅቶች አንዱ ነው።