የኢትዮጵያ ፓስፖርቶች እና የጉዞ ሰነዶች ዘመኑን የዋጁ እና የደህንነት ባህሪያት እንዲኖራቸው መደረጉ ትልቅ እመርታ ነው- ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀሥላሴ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ፓስፖርቶች እና የጉዞ ሰነዶች ዘመኑን የዋጁ እና የደህንነት ባህሪያት እንዲኖራቸው መደረጉ ትልቅ እመርታ ነው- ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀሥላሴ

AMN – የካቲት 14/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ፓስፖርቶች እና የጉዞ ሰነዶች ዘመኑን የዋጁ እና የተራቀቁ የደህንነት ባህሪያት እንዲኖራቸው መደረጉ ትልቅ እመርታ ነው ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀሥላሴ ገለጸዋል።

ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በኢትዮጵያ የተመረተ አዲስ ኢ-ፓስፖርት ዛሬ ይፋ ተደርጓል፡፡

በዚሁ ወቅት ፕሬዝደንት ታዬ አፅቀሥላሴ፣ የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት ተግባራዊ መደረጉ የሀገርን ገጽታ ከመገንባት ባሻገር ለዜጎች የተሰጠውን ዋጋ የሚገልፅ ነው ብለዋል።

ፓስፖርቱ ማንኛውንም አይነት ማጭበርበር ለመግታት የማይተካ ሚና እንደሚኖረው ፕሬዚዳንት ታየ ተናግረዋል።

ዘመናዊ ሰነዶች የሰዎችን እንቅስቃሴ ከማፋጠን ባሻገር ንግድን ለማሳለጥና ህጋዊ የስራ ዕድል ለማግኘት አስፈላጊ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ኢ-ፓስፖርቱ ለዜጎች ጥራት እና ግልፅነት የተላበሰ አገልግሎት ለመስጠት ያግዛል ብለዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት በበኩላቸው፣ ኢ-ፓስፖርቱ የአንድን ግለሰብ ባዮሜትሪክ መረጃ ጨምሮ የጣት አሻራዎችን፣ የፊት ለይቶ ማወቂያ እና የኤሌክትሮኒክስ ቺፕስ ያካተተ እንደሆነ ገልፀዋል።

ኢ-ፓስፖርቱ የኢሚግሬሽን ሂደቶችን ማቀላጠፍን ጨምሮ ሀሰተኛ መረጃዎችን እና ማጭበርበርን ለመከላከል የሚያስችል የላቀ የደህንነት ባህሪያትን ያካተተ መሆኑንም ገልጸዋል።

በተጨማሪም ሀሰተኛ ፓስፖርቶችን የመስራት ወይም የሌላ ሰው ፓስፖርትን ላልተገባ ዓላማ የመጠቀም ስጋቶችን እንደሚቀንስም አረጋግጠዋል።

ከዚህም ባሻገር የኢትዮጵያን የአየርና የየብስ ድንበሮች በአግባቡ ለመቆጣጠር እና የሀገር ደህንነትን ከመጠበቅ አኳያ ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review