የኢትዮጵያን አየር ሃይል በሁሉም ረገድ በዘመናዊ መልኩ በመገንባት የሀገር አለኝታ የሆነ ጠንካራ ተቋም ማድረግ ተችሏል -ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ

AMN-ኅዳር 19/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያን አየር ሃይል በሁሉም ረገድ በዘመናዊ መልኩ በመገንባት የሀገር አለኝታ የሆነ ጠንካራ ተቋም ማድረግ መቻሉን የአየር ሃይሉ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል 89ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በተለያዩ መርሃ ግብሮች በነገው ዕለት ያከብራል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ፤ አየር ሃይሉ ከለውጡ በኋላ በቁጭትና በከፍተኛ ጥረት በዘመናዊ መልኩ መገንባቱን ገልጸዋል።

የአየር ሃይሉ የግንባታ መሰረትም በብቁ የሰው ሃይል፣ በዘመናዊ ትጥቅና ቴክኖሎጂ የተደራጀ መሆኑን ነው የተናገሩት።

የአየር ሃይሉን ነባር አውሮፕላኖችና ቴክኖሎጂዎች በማሻሻል እንዲሁም አዲስ በማምረት በሁሉም ረገድ ዘመኑ የደረሰበት የሀገር አለኝታ የሆነ ጠንካራ ተቋም መገንባት ችለናል ብለዋል።

በለውጡ ዓመታት በጥናት ላይ በመመርኮዝ ቴክኖሎጂ በሚሸከም የሰው ኃይል፤ በዘመናዊ ትጥቅ፣ በውጊያ መሰረተ ልማት እንዲሁም አየር ኃይሉ ለሁሉም መስክ ምሳሌ የሆነ ተቋም በሚያደርጉ ሥራዎች ላይ በትኩረት መሰራቱን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review