የኢትዮጵያዊነት ምንነት ላይ ሳንግባባ በሌሎች ጉዳዮች ላይ መነጋገር አስቸጋሪ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ

You are currently viewing የኢትዮጵያዊነት ምንነት ላይ ሳንግባባ በሌሎች ጉዳዮች ላይ መነጋገር አስቸጋሪ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ

AMN- ግንቦት 27/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያዊነት ምንነት ላይ ሳንግባባ በሌሎች ጉዳዮች ላይ መነጋገር አስቸጋሪ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢቲቪ ጋር ባደረጉት ልዩ ቆይታ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምልከታቸውን አጋርተዋል።

የኢትዮጵያዊነት ምንነት ላይ ሳንግባባ በሌሎች ጉዳዮች ላይ መነጋገር አስቸጋሪ መሆኑን በማንሣትም፣ የኢትዮጵያውያን ሕብር ማንነቶች የመለያየት ምክንያት እንዳይሆኑ እንደ አንድ ቤተሰብ የሚያደርግ አሰባሳቢ ትርክት ያስፈልጋል ብለዋል።

“ማንኛውንም ትልሞቻችን ልናሳካ የምንችለው በግዙፉ የኢትዮጵያዊነት ማንነት ውስጥ ነው፤ ኢትዮጵያዊነት አሰባሳቢ ትርክት ነው” ሲሉም ነው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።

በአሰባሳቢው የኢትዮጵያዊነት ማንነት ውስጥ ቀጣይ ትልሞችን ለማሳካት ለነገ የሚሆን እና ብሔራዊ ጥቅምን ያስቀደመ ሥራ መሥራት እንደሚገባም አብራርተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review