የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታየ አፅቀሥላሴ የሮም ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያ ሊቀጳጳስ ፍራንሲስ ህልፈት የተሰማቸው ሀዘን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቅድስት ልደታ ማሪያም ካቴድራል ቤተ-ክርስቲያ ለሊቀጳጳስ ፍራንሲስ የፀሎት እና ፈታት መረኃ-ግበር ተከናውኗል፡፡
በመረኃ-ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታየ አፅቀሥላሴ በመታደም የተሰማቸው ሀዘን ገልጸዋል፡፡
የሊቀጳጳስ ፍራንሲስ ቀን ለጎደለባቸው ጋሻ መከታ በመሆን በፀሎታቸው በማስታወስ እና በመባረክ ታላቅ መንፈሳዊ አገልግሎት የሰጡ አባት ናቸው ብለዋል ፕሬዝዳንት ታየ፡፡
ከተገፉ ጎን የሚቆሙ፣ ለሰላም ሲሰሩ የነበሩ ታላቅ አባት ናቸው ያለቱ ፕሬዝዳንት ታየ አፅቀሥላሴ፣ ለግፉዓን ጠበቃ በመሆናቸው በዓለም ዙሪያ መከራ ለጎበኛቸው ሁሉ ጠበቃ፣ ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ በመሆን ለ12 ዓመታት የዓለምን ህዝብ በቅንነት እና በበጎነት ያገለገሉ አባት ናቸው ብለዋል፡፡
እኒህ አባት በተለይ ጦርነት በተከሰተባቸው እና ሰላም ባጡ አካባቢዎች ሁሉ ፈጥኖ ደራሽ ነበሩ በማለትም ተናግረዋል፡፡
በአልማዝ ሙሉጌታ