የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሚኒስትሩ፣ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር፣ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ የሁለትዮሽ ግንኙነትን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡