የኦሮሚያ ክልል 1 ሺህ 402 የግብርና ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች አስረከበ

You are currently viewing የኦሮሚያ ክልል 1 ሺህ 402 የግብርና ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች አስረከበ

AMN- መጋቢት 29/2017

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት 1 ሺህ 402 የግብርና ትራክተሮችን ከነ ሙሉ መለዋወጫዎቹ ለአርሶ አደሮች፣ ለህብረት ስራ ማህበራት እና ዩኒየኖች በዛሬው እለት በሻሸመኔ ከተማ አስረክቧል።

የክልሉ መንግስት ምርት እና ምርታማነትን ለማሳድግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

ትራክተሮቹን የተረከቡት አርሶ አደሮች የህብረት ስራ ማህበራት እና ዩኒየኖች ለክልሉ መንግስት ጥያቄ ያቀረቡ እና ቀድመው የቆጠቡ መሆናቸው ተገልጿል።

ትራክተሮቹ ኬኛ የግብርና መሳሪያዎች ማምረቻ እና ጠቅላላ ንግድ ሀላፊነቱ የተወሰነ ድርጅት በሀገር ውስጥ የተገጣጠሙ ናቸው።

ትራክተሮቹ የክልሉ መንግስት የግብርና ሜካናይዜሽንን ለማስፋፋት ለያዘው ዕቅድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል ተብሏል።

የትራክተሮቹ ርክክብ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት መከናወኑን ከፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review