AMN – ታኅሣሥ 14/2017 ዓ.ም
ፓሪስ
የፓሪስ የህዝብ ቁጥር ከ2 ሚሊየን 161ሺህ በላይ እንደሚሆን ይገመታል፡፡
የከተማዋ የቆዳ ስፋት 2.5 ስኩየር ኪሎ ሜተር ስኩየር እንደሚበልጥ ይታመናል።
እ.ኤ.አ. ከ1399 እስከ 1411 ዓ.ም. ድረስ የዛሬዋን ፓሪስ የቀድሞዋን ቡርጎኝ ከተማን ለመያዝ ነገስታት ይዋጉ ነበር።
እ.ኤ.አ. በ1428 የእንግሊዝ ንጉሥ ፓሪስ ተቆጣጠረ።
የፈረንሳዩ ንጉሥ ፓሪስን ነጻ ካወጣ በሗላ ፓሪስ የፈረንሳይ ዋና ከተማነቷን ይዛ ቀጥላለች።
ፓሪስ በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በክርስትና እምነት ተከታይ የነበረች ሲሆን ከሮማን ኢምፓየር ውድቀት በኋላ ዋና ከተማዋ በፍራንካውያን ንጉስ ክሎቪስ ተይዛለች።
እ.ኤ.አ. 250 እስከ 225 ዓ.ዓ. መካከል የሴልቲክ ሴኖኔስ ንኡስ ጎሳ የሆነው ፓሪስ በሴይን ዳርቻ ላይ ሰፍሮ ድልድይ እና ምሽግ ገንብቶ በአውሮፓ ከሚገኙ መንደሮች ጋር የንግድ ልውውጥ መጀመሩ ይነገራል።
ፓሪስ በአንደኛው የዓለም ጦርነት እና በጀርመን ወረራ እንዲሁም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የቦምብ ድብደባ ደርሶባታል፡፡
የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያን ተከትሎም አብዛኞቹ ኢንደስትሪዎች ስራ አቁመዋል ፣ የመኖሪያ ቤቶች እጥረት እና የምግብ አቅርቦት ችግርም ተከስቶ እንደነበር ይነገራል።
በናፖሊዮን III እና በሴይን ግዛት ዋና አስተዳዳሪ በጆርጅ-ኢዩጂን ሃውስማን እ.ኤ.አ. በ1852 እና 1870 መካከል አደባባዮች እና መናፈሻዎች በአዲስ መልክ ተገንብተው ከተማዋ አሁን ባለችበት ደረጃ ተስፋፍታለች።
ፓሪስ በመካከለኛው ዘመን፣ በአውሮፓ አለች የምትባል ትልቋ ከተማ ስትሆን፣ የሀይማኖት እና የንግድ ማእከል እንዲሁም የጎቲክ የስነ-ህንፃ ዘይቤ የፈለቀባት ከተማም ነበረች።
ፓሪስ የዘመናዊ ጥበብ ዋና ከተማ እና በዓለም ዙሪያ ላሉ ምሁራን፣ ጸሃፊዎች እና አርቲስቶች መገናኛ ከተማም ነበረች።
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቱሪስቶች የፓሪስን ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽኖች እና የኢፍል ግንብን ለማየት በየቀኑ ይጎርፋሉ ።
ምንጭ:- ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካና ሌሎች ድረ ገጾች
በሽመልስ ታደሰ