የከተራ በዓል በመላ አገሪቱ እየተከበረ ነው

You are currently viewing የከተራ በዓል በመላ አገሪቱ እየተከበረ ነው

AMN – ጥር 10/2017 ዓ.ም

የከተራ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ዘንድ በዛሬው ዕለት እየተከበረ ይገኛል።

ታቦታት ከየአብያተክርስቲያናቱ ወጥተው ወደየማደሪያቸው ባሕረ-ጥምቀት በማምራት ላይ ይገኛሉ።

በመዲናችን አዲስ አበባም በዓሉ ጃንሜዳን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች እየተከበረ ነው።

በጃንሜዳ በሚከበረው የከተራ በዓል ላይ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች እና ቱሪስቶች እየታደሙ ነው።

በከተራ ዕለት ወደ ባሕረ ጥምቀቱ የሚደረገው ጉዞ ኢየሱስ ክርስቶስ ከልዕልና ወደ ትህትና መውረዱን የሚያሳይ መንፈሳዊ እሴት ሲሆን ይህም ምዕመናን በፍቅርና በትህትና መኖር እንደሚገባቸው የሚያስተምር መሆኑን የሃይማኖት አባቶች ይገልጻሉ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review