AMN- ጥር 23/2017 ዓ.ም
የኩባ ኮሙኒስት ፓርቲ እና የተርኪሚንስታን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት በብልጽግና ፓርቲ ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
የኩባ ኮሙኒስት ፓርቲ ማእከላዊ ጽህፈት ቤት አባል ዩዲ መርቼዲስ ሄርናንዴዝ በብልጽግና ፓርቲ ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
እንዲሁም በተርኪሚንስታን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ ክፍል ተጠሪ እና የልዑካን ቡድኑ መሪ ያዝጉሊ ማሜዶቭ እንዲሁም ሌሎች የፓርቲው አመራሮች እና አባላት በብልጽግና ሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
እንግዶቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል እንዳደረጉላቸው ኢዜአ ዘግቧል።
የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ከዛሬ ጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡