
AMN ታህሳስ -2/2017 ዓ.ም
የኬንያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ አመራሮችና የኮሌጁ ሰልጣኞች ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተገኝቶ ጉብኝት አድርጓል፡፡
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሀሰን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተገኝተው የአየር መንገዱን የተለያዩ አገልግሎቶችና መሠረተ ልማቶችን አስጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የአየር መንገዱን የካርጎ ተርሚናል፣ የበረራ መማርያ ሲሙሌተር፣ የአየር ትራፊክ ቁጥጥር ስራንና ሌሎችንም አገልግሎቶች ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው የአየር መንገዱን መሠረተ ልማት በማስፋፋትና የዘርፉን ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ በማዋል አገልግሎቶችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በተሰራው ስራ ውጤታማ ሆነናል ብለዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ለማስተሳሰርና ከዓለም ጋር ለማገናኘት እየሰራ እንደሆነም ጨምረው ገልፀዋል።
የልካን ቡድኑ አባላት በነበራቸው ትምህርታዊ ጉብኝት መደሰታቸውንና ጠቃሚ ተሞክሮ ማግኘታቸውን ገልፀዋል።
በተጨማሪም ስለተደረገላቸው አቀባበልና ስላገኙት እንክብካቤ ምስጋና ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።