የወል ትርክት ለማህበረሰብ ግንባታ መሰረታዊ በመሆኑ በኪነ ጥበብ በመታገዝ የማስረፅ ስራ ቀጣይነት እንደሚኖረው የአዲስ አበባ ባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) ገልዋል፡፡
‹‹የወል ትርክት ለነገዋ ኢትዮጵያ ተስፋ በአዲሱ ትውልድ እውን ይሆናል›› በሚል መሪ ቃል የስነ ጽሁፍ ምሽት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተካሂዷል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) ነጠላ ትርክት ነጣጣይ እና ከፋፋይ በመሆኑ የወል ትርክትን በማስረጽ ውስጥ አንድነትን ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡
ኪነ-ጥበብን በመጠቀም በሀገር ግንባታ ላይ ከፍተኛ አበርክቶ ያለውን የወል ትርክት የማስረጹ ስራ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
በትባረክ ኢሳያስ