የወጣቶችን ኢኮኖሚያ ተጠቃሚነት እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ጠንካራ አደረጃጀት ተገንብቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing የወጣቶችን ኢኮኖሚያ ተጠቃሚነት እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ጠንካራ አደረጃጀት ተገንብቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

AMN- ሚያዝያ 16/2017 ዓ.ም

የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ዋና ፅ/ቤት የ3ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል።

ወጣቶች የነገ ሀገር ተረካቢዎች ብቻ ሳይሆኑ የዛሬ አቅሞች በመሆናቸው ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶችን ወደ አመራርነት በማምጣት ለሀገራቸው ብልጽግና የጎላ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ እያደረገ መሆኑን የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ገልፀዋል።

የብልፅግና ፓርቲ የወጣት ክንፍ ምከትል ፕሬዝዳንት አባንግ ኩሙዳን ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት ሂደት ውስጥ የወጣት ክንፉ ጠንካራ ሚና እየተወጣ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

በየክልሎቻቸው ያሉ ወጣቶች ስራ እንደፈጠረላቸው እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው ከፍ እንዲል መስራታቸውን የገለፁት ደግሞ የግምገማው ተሳተፊ የወጣት ክንፍ አመራሮች ናቸው።

የወጣቶች የፖለቲካ ተሳትፎ እያደገ መምጣቱም የተገለፀ ሲሆን ወደ አመራርነት ሚና የሚመጡ ወጣቶች ቁጥርም ከፍ ብሏል ነው የተባለው።

ወጣቶች ሰላምን በመጠበቅ ረገድ ከፍ ያለ ሚና ስላላቸው ፤ የሰላም እጦት ባለባቸው አካባቢዎች የፓርቲው የወጣት ክንፍ ወጣቱን በማወያየት በሰላማዊ አማራጭ ችግሮች እንዲፈቱ እየተሰራ መሆኑም ተመልክቷል።

በአሰግድ ኪዳነማርያም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review