የውጭ ምንዛሬ ተመን ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ የብሔራዊ ባንክን የውጭ ምንዛሬ መጠባበቂያ ክምችት 200 በመቶ ጨምሯል- የባንኩ ገዥ ማሞ ምህረቱ

You are currently viewing የውጭ ምንዛሬ ተመን ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ የብሔራዊ ባንክን የውጭ ምንዛሬ መጠባበቂያ ክምችት 200 በመቶ ጨምሯል- የባንኩ ገዥ ማሞ ምህረቱ

AMN -መጋቢት 23/2017

በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ተመን ማሻሻያ መደረጉን ተከትል የብሔራዊ ባንክ ውጭ ምንዛሬ መጠባበቂያ ክምችት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 200 በመቶ መጨመሩን የባንኩ ገዥ ማሞ ምህረቱ ገለፁ።

የውጭ ምንዛሬ ተመን አስተዳድር ማሻሻያው የውጭ ምንዛሬ ፍሰት እንዲጨምር እና ቀድሞ የነበረው የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንዲቃለል ማድረጉን አንስተዋል።

ባንኩ ከረጅም ዓመታት በኋላ ሀምሌ 2017 ዓ.ም የውጭ ምንዛሬ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውሰው፤ ይህም የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬ ስርዓት እንዲኖር እና የነበረው እጥረት እንዲቃለል ማስቻሉን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የብሔራዊ ባንክ መጠባባቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት መጨመሩን አንስተዋል።

ከማሻሻያው ወዲህ የባንኩ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት በ200 በመቶ ማደጉን ተናግረው፤ ይህም የባንኩን የዕቅዱን ቀድሞ ማሳካት መቻሉን ጠቅሰዋል።

ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሬ አስተዳደር መመሪያዎች አፈጻጸም ሂደት ዙሪያ ከባንኮች ስራ አስፈጻሚዎች ጋር ሰፊ ውይይት ማድረጉን ገልጸዋል።

በዚህም በአጻጸም ሂደት የሚስተዋሉ አንዳንድ ክፍተቶች እንዳሉ ጠቅሰው፤ እነዚህ ክፍተቶች እንዲስተካከሉ መመሪያ መስጠቱን ተናግረዋል።

ለአብነትም ባንኮች የሚያስከፍሉት የአገልግሎት ክፍያ ተመጣጣኝ የማድረግ፣ለግል ዘርፍ የውጭ ምንዛሬ እንዲያቀረቡና መመሪያዎች በቅጡ እንዲተገበር መግባባት ላይ ተደርሷል ነው ያሉት።

የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬ ተመን እንዲኖር ብሔራዊ ባንክ በየሁለት ሳምንቱ ግልጽ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ እንደሚያካሂድ ገልጸዋል።

በሕገ ወጥ መንገድ የውጭ ምንዛሬ ግብይት በሚያካሄዱ: በሚያሸሹና በሚያዘዋውሩ ኩባንያዎችና ግለሰቦች ላይ ከፀጥታ ተቋማት ጋር በመተባበር ጥብቅ ቁጥጥርና እርምጃ እንደሚወስድ አሳስበዋል።

ሕገ ወጥና ፈቃድ የሌላቸው የውጭ ምንዛሬ አዘዋዋሪዎች ኩባንያዎችና ግለሰቦች ከኢትዮጵያ ባንኮች ጋር የሚተሳሰሩበት መንገድ ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

ህብረተሰቡ ከእነዚህ ህገ ወጥ አካላት በመራቅ ራሱን ከአደጋና ከመጭበርበር እንዲብቅ ጥሪ ማቅረባቸዉን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review