AMN – ታኅሣሥ 10/2017 ዓ.ም
የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ መፈቀዱ ለኢትዮጵያ አዲስ ምዕራፍ ነው ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም አስታወቁ።
እርምጃው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አመራር ሰጪነት እየተከናወነ ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና ሊበራላይዜሽን ጥረት አካል እንደሆነም ጠቁመዋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት እንዲሆን የሚያስችለውን አዋጅ ማፅደቁ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ አዲስ ምዕራፍ መሆኑንም ኃላፊዋ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ጠቅሰዋል።