የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

You are currently viewing የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

AMN – የካቲት 7/2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ፓርላሜንታሪ ምክትል ሚኒስትር ኤሪ አርፊያ ጋር በሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

አምባሳደር ምስጋኑ ኢትዮጵያ እየተገበረችው ያለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሰፊ የኢንቨስትመንት ዕድል የፈጠረ በመሆኑ የጃፓን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት እንዲሠማሩ ጠይቀዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው የቀይ ባሕር እና የአፍሪካ ቀንድ የደህንነት ስጋት ቀጣናዊ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ የጋራ ደህንነት ሰጋት መሆኑን በመግለጽ፣ ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት እያደረገች ያለውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል።

ጃፓን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነት የበለጠ በኢኮኖሚ ግንኙነት አጠናክራ እንድትቀጥል እና መንግሥታዊ የልማት ድጋፏንም እንድታጠናክር ጠይቀዋል።

የጃፓን የውጭ ጉዳይ ፓርላሜንታሪ ምክትል ሚኒስትር ኤሪ አርፊያ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት ቁልፍ አገር መሆኗን ገልጸዋል።

ጃፓን ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት እያደረገች ያለውን ከፍተኛ አበርክቶ ታደንቃለች ብለዋል።

ምክትል ሚኒስትሯ አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት የበለጠ አጠናክራ እንደምትቀጥል ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review