AMN-ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከኖርዌይ ፍትህ ሚኒስትር ኤምሊ ኧንገር መኸል ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡
ኖርዌይ የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ አጋር ሀገር መሆኗን የገለጹት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፤ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ተግባራዊ እያደረገችው ያለችው የኢኮኖሚ ሪፎርም ለውጭ ኩባንያዎች የተሻለ የተሳትፎ ዕድል መፍጠሩንም ጠቁመዋል፡፡
በዚህም የኖርዌይ ባለሐብቶች መዋዕለ ነዋያቸውን በኢትዮጵያ እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል።
የፍትህ ሚኒሰትሯ በበኩላቸው ኖርዌይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗን መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡