የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስታሊና ጂኦርጂዬቫ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

You are currently viewing የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስታሊና ጂኦርጂዬቫ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

AMN – የካቲት- 2/2017 ዓ.ም

የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስታሊና ጂኦርጂዬቫ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።

ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ ከገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ፣ ከብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ፣ ከፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) እና ከሌሎች የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር የአድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።

ክርስታሊና ጂኦርጂዬቫ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው የስራ ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት፣ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ፖሊሲዎች፣ በኢኮኖሚ ማሻሻያዎችና በግሉ ዘርፍ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድሎች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ የስራ ጉብኝታቸውም አይኤምኤፍ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ልማት ለመደገፍ እና የፖሊሲ ምክክሮችን በማድረግ የማይበገር እና ዘላቂ ሀገራዊ ብልጽግናን ለማምጣት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ ተመላክቷል።

ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ በትላንትናው ዕለት ብሔራዊ ቤተ መንግሥትን፣ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከልን እና ብርሃን የዓይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤትን መጎብኘታቸው ይታወቃል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review