የዓድዋ ኃያል መንፈስ

You are currently viewing የዓድዋ ኃያል መንፈስ

1. የዓድዋ ድል-ከጦርነት ድል በላይ

የዓድዋ የጦርነት ፍልሚያ ብቻ አይደለም ። ዓድዋ ዘመን ተሻጋሪ የሆነ ደማቅ አሻራ ነው ።

በዘመናት መካከል እምቢኝ ለቅኝ አገዛዝ ማለት የቻለ የጥቁር ህዝብ ታሪክ የተፃፈበት፣ ትውልድን ያነቃቃ፣ የድል አድራጊውን ሀገርና ህዝብ ማንነትና ምንነት ለዓለም ያስመሰከረ ነው፡፡ ዛሬም ድረስ በትውልድ መካከል የሚያስተጋባ የአሸናፊነት ድምፅ ነው፡፡ የዓድዋ አሻራ ፡፡

የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በአፍሪካ ብቸኛው በቅኝ ግዛት ሥር ያልወደቀ ህዝብ ጣሊያንን ድባቅ መቶ ዓለምን አስደምሟል። ይህ ከጦርነት ድል በላይ ነው ። አፍሪካ የአንድነት እና የጥንካሬዋ መገለጫም ጭምር ነው ።

2. ዓድዋ እና ፓን አፍሪካኒዝም

የዓድዋ ድል ለዓለም ያስተላለፈው ሌላኛው መልዕክት አፍሪካ ቅኝ ገዥነትን የማትቀበል መሆኗን ነው ።ከማርኮስ ጋርቬይ እስከ ኩዋሜ ንኩሩማ ያሉ መሪዎችም ኢትዮጵያ የአፍሪካ ተስፋ ምልክት መሆኗን አወጁ። ፓን አፍሪካኒዝምን ያቀነቅኑ ዘንድም ጀመሩ። የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በአህጉሪቱ ላሉ ፓን አፍሪካኒስቶች እና የነፃነት ታጋዮች የኩራት ምንጭ ሆነላቸው።

3.የዓድዋ ሚና ለዘመናዊት ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያዊያን በየዓመቱ የዓድዋን በዓል በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት ያከብራሉ። ታዲያ በዓሉን የሚያከብሩት ለታሪክ ማስታወሻነት ብቻ አይደለም፣ ይልቁንም ከዓድዋ ድል ጀርባ ያለውን ኃያል አንድነትን ለማስታወስ እና አጠናክሮ ለማስቀጠልም እንጅ።

4.ዛሬም ያልሞተው የዓድዋ መንፈስ

ዓድዋ የጥንቱ ዘመን የአንድ ወቅት ታሪክ ብቻ አይደለም። ዓድዋ የነፃነት፣የአንድነት እና የጥንካሬ እሳቤ ነው ።ኢትዮጵያ በየዘመናቱ ለሚያጋጥማት ፈታኝ ሁኔታዎች የአንድነት መሣሪያ ሆኖ አንድነቷን አጠንክሯል።ለመጪው ትውልድም የዓድዋ መንፈስ የአንድነት መመሪያ ሆኖ ይቀጥላል።

5. ሊነገር፣ ሊከበር፣ ሊዘከር የተገባው

የዓድዋ አሻራ በሁሉም ኢትዮጵያውያን እና በነፃነት በሚያምኑ አፍሪካዊያን ልብ ውስጥ ዛሬም ህያው ነው።

ሊነገር፣ ሊከበር፣ ሊዘከር እና ለትውልድ ሊተላለፍ የተገባው ነው ።

የዓድዋን ሀያልነት በልኩ የተገነዘበው የኢትዮጵያ መንግስትም መታሰቢያውን በመሀል አዲስ አበባ ታሪኩን በሚመጥነው መልኩ ገንብቶ ለትውልድ አስቀምጧል።

አሁን ያለው እና የሚመጣው ትውልድም የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን በተመለከተ ቁጥር ሳይነገረው ሳይተረክለት ኢትዮጵያዊነቱ፣ አፍሪካዊነቱ እና ከድሉ ጀርባ ያለውን የአያቶቹን ጠንካራ ክንድ እና ሀገር ወዳድነት ይገነዘባል፡፡ እሱም በዘመኑ ለሀገሬ ምን ላበርክት ብሎ እንዲያስብ ያነሳሳዋል፡፡

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review