AMN – የካቲት 20/2017 ዓ.ም
ከፊታችን የሚከበረውን የዓድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ለጎብኝዎች ክፍት ሆኖ በነጻ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገለጸ፡፡
በበዓሉ ዋዜማ ቅዳሜ የካቲት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እሰከ ቀኑ 11፡00 ድረስ ማንኛውም ሰው ወደ ዓድዋ መታሰቢያ በነፃ በመግባት መጎብኘት እንደሚችል ማዕከሉ አስታወቋል፡፡
በዕለቱም መላው ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ በቦታው በመገኘት ጉብኝት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡
129ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በመጪው እሁድ የካቲት 23 እንደሚከበር ይታወቃል፡፡