የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በተለያዩ የጤና ሳይንስ እና ህክምና ዘርፎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 186 ተማሪዎችን አስመረቀ።

You are currently viewing የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በተለያዩ የጤና ሳይንስ እና ህክምና ዘርፎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 186 ተማሪዎችን አስመረቀ።

AMN – መጋቢት 13/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሽታን የመከላከል እና አክሞ የማዳን ፖሊሲን ለመተግበር ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ መሆኑን በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

በሽታን ከመከላከል አንጻር ከተማዋ ንጹህ፣ ለኑሮ ምቹ እና ከብክለት የጸዳች ብሎም አረንጓዴ እንድትሆን እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ከንቲባ አዳነች፣ ከህጻናት ጤና አንጻርም አዲስ አበባን ህጻናት ቦርቀው በአካልም በአዕምሮም ጎልብተው የሚያድጉባት ህጻናትን ለማሳደግ ምቹ አፍሪካዊት ከተማ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

አክሞ ከማዳን አንጻርም አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የሚያስችሉ የአዳዲስ ሪፈራል ሆስፒታሎች ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን የተናገሩት ከንቲባ አዳነች፣ በነባር ሆስፒታሎችም አገልግሎታቸውን የበለጠ ማላቅ እና ማሳደግ እንዲችሉ የተለያዩ የማስፋፊያ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልዋል፡፡

የጤና ተቋማቱን በዘመናዊ የህክምና መሣሪያዎች እና ቴክኖሎጂ ለማሟላት ከግሉ ዘርፍ ጋር በመተባበር ጭምር እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።

የህክምና ተቋማትን ማስፋፋትና በመሳሪያ ማሟላት ብቻ በቂ አይደለም ያሉት ከንቲባ አዳነች፣ በዘርፉ ብቁ ባለሞያዎችን ለማፍራት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የየካቲት 12 ሜዲካል ኮሌጅም ይህንን ክፍተት ለመሙላት እና በተለያዩ የህክምና መስኮች ብቁ ባለሞያዎችን አሰልጥኖ እያበቃ መሆኑን ገልጸዋል።

ተመራቂዎች በቅንነት እና በታማኝነት ማህበረሰባቸውን እንዲያገለግሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በሰብስቤ ባዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review