የገና፣ ጥምቀት እና የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በጥሩ ሁኔታ እንዲከበሩ አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት

AMN – ታኅሣሥ 25/2017 ዓ.ም

የገና፣ ጥምቀት እና የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በጥሩ ሁኔታ ተከብረው እንዲያልፉ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የበዓላት ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ተፈራ ሞላ ዉሃ፣ ኤሌትሪክ፣ እሳት እና አደጋ፣ጽዳት፣ መብራት እና መሰል ጉዳዮች ላይ አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ተግባራት በእቅድ እንዲመሩ እየተደረገ መሆኑን የጠቆሙት ምክትል ኃላፊው ችግሮች ካጋጠሙ በተለያዩ አማራጮች ማሳወቅ እና መፍትሄ ማግኘት ይቻላል ብለዋል።

በዓሉ በተሻለ መልኩ እንዲጠናቀቅ ህዝቡ አጋርነቱን ማሳየት እንዳለበትም ጠቁመዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በበኩሉ በአሉ ውብ በሆነ ስፍራ እንዲከበር ከተለያዩ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

ከወዲሁ የተለያዩ ተረፈ ምርቶችን እያስወገደ መሆኑን የገለጸው ኤጀንሲው፣በበአላት ወቅት የሚመነጩ ተረፈ ምርቶችን ለማስወገድ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓልም ብሏል።

ህዝቡም ተረፈ ምርቶችን በአግባቡ ለሚመለከተው አካል ሊሰጥ ይገባል ሲልም ገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የኢየሱስ ክርስቶ የልደት በዓል ገና፣ጥምቀት እና የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ያለምንም አደጋ እንዲጠናቀቅ በልዩ ሁኔታ ሰራተኞች እንዲሰለጠኑ እና ወደስራ እንዲገቡ መደረጉን ገልጿል።

አደጋዎች ሲፈጠሩ በቂ ምላሽ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን እና ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መከናወኑንም አስታወቋል።

ማህበረሰቡ በበኩሉ በአሉን ሲያከብር ለአደጋ ከሚዳርጉ ተግባራት በመቆጠብ ሊሆን እንደሚገባ አመላክቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ መብራት አገልግሎት ባለስልጣንም በተመሳሳይ አስፈላጊውን ዝግጅት መደረጉን ገልጾ ችግሮች ካጋጠሙ በተለያዩ አማራጮች ማሳወቅ እና መፍትሄ ማግኘት እንደሚችል አስታውቋል።

በሃብታሙ ሙለታ

+2

All reactions:

3636

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review