የጋራ ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን መቋቋሙ በአፍሪካ ቀንድ እና በምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ የንግድ ትስስርን እና ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ያሳድጋል- አለሙ ስሜ (ዶ/ር)

You are currently viewing የጋራ ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን መቋቋሙ በአፍሪካ ቀንድ እና በምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ የንግድ ትስስርን እና ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ያሳድጋል- አለሙ ስሜ (ዶ/ር)

AMN – የካቲት 21/2017 ዓ.ም

ከትናንት በስትያ የጀመረው የኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን ምስረታ ሚንስትሮች መድረክ የጅቡቲ፣ ኢትዮጵያ፣ደቡብ ሱዳን፣ ዩጋንዳ ኮሪደር ባለስልጣን መመስረቻ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል።

ስምምነቱ በአፍሪካ ቀንድ እና በምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ የንግድ ትስስርን እና ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ለማሳደግ እንደሚያስችል የትራንስፓርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ፣ ይህ ኮሪደር ለጋራ ብልፅግና አይነተኛ ሚና እንደሚኖረው በመረዳቷ ፈጣን ትግበራ ለማካሄድ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጣለች ብለዋል ሚኒስትሩ።

ሚኒስትሩ አክለውም ኮሪደሩ በሎጅስቲክስ ለመደጋገፍ፣ ለተሻሻለ ትብብር እና ለየሀገራቱ ብሩህ የወደፊት የተስፋ መንገድ የሚከፍት እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review