የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ከኖርዌይ አምባሳደር ጋር በካርቦን ሽያጭ ዙሪያ ተወያዩ

AMN ህዳር 23/2017 ዓ.ም

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር ስቲያን ክሪስተንሰን ከተመራ የልዑክ ቡድን ጋር በኢትዮጵያ ስላለው ተጨባጭ የካርቦን ሽያጭ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በተፋሰስ ልማትና በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር የተራቆቱ አካባቢዎች ለምተው በደን በመሸፈናቸው ዘርፈ-ብዙ ፋይዳዎች የተገኙ ሲሆን ከነሱ መካከል የካርቦን ሽያጭ አንዱ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በዚህም በየክልሎቹ የተደራጁ የደን ማህበራት የካርቦን ሽያጭ በማድረግ ተጨማሪ ገቢ እያገኙም ይገኛሉ፡፡

በዛሬው ዕለትም የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር ስቲያን ክሪስተንሰን ከተመራ ልዑክ ቡድን ጋር በኢትዮጵያ ስላለው ተጨባጭ የካርቦን ሽያጭ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በክልሎች ያለውን የካርቦን ሽያጭ ተሞክሮን ሀገራዊ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ እንዲሁም በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተው የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡

በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ተግባራቶች ላይም የተወያዩ ሲሆን፤ በዚህ ጉዳይ ኢትዮጵያ ይበልጥ ውጤታማ እንድትሆን ወደፊት በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review