የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በቅዳሜ እና እሁድ የገበያ ማዕከላት በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረቡ ነው- የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ

You are currently viewing የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በቅዳሜ እና እሁድ የገበያ ማዕከላት በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረቡ ነው- የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ

AMN – መጋቢት 6/2017 ዓ.ም

የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በመዲናዋ በቅዳሜ እና እሁድ የገበያ ማዕከላት በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረቡ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ገለጸ፡፡

ሸማቾችም የግብርና እና ኢንዱስትሪ ምርቶችን አቅራቢያ ከሚገኙ የቅዳሜ እና እሁድ የገበያ ማእከላት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸምቱ አመላክቷል።

በየክፍለ ከተማው የኑሮ ዉድነትን በማረጋጋት ትልቅ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ የሚገኘው የሰንበት ገበያ የተለያዩ ጥራት ያላቸዉ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ቀርበው እንደሚገኙም ነው ቢሮው የጠቆመው።

ይህም ለህብረተሰቡ አማራጭ የገበያ ቦታ በመሆን በስፋት ግብይት እየተከናወነ መሆኑን መመልከት መቻሉን የቢሮው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review