የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቬይትናም ጉብኝት የሀገራቱን ግንኙነት የሚያጠናክርና ተሞክሮ የተቀሰመበት ነው-ቢልለኔ ስዩም

You are currently viewing የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቬይትናም ጉብኝት የሀገራቱን ግንኙነት የሚያጠናክርና ተሞክሮ የተቀሰመበት ነው-ቢልለኔ ስዩም

AMN- ሚያዝያ 13/2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በቬይትናም ያደረጉት ጉብኝት የሀገራቱን ግንኙነት የሚያጠናክርና ተሞክሮ የተቀሰመበት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊ ቢልለኔ ስዩም ገለጹ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊ ቢልለኔ ስዩም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት በቬይትናም ያደረጉትን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በማብራሪያቸውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቬይትናም ቆይታቸው ከሀገሪቱ የተለያዩ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር መምከራቸውን አስታውቀዋል፡፡

በዚህም በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ ዘርፎች ያለውን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር የሚያስችል ውይይት መደረጉን ነው ያብራሩት፡፡

የቬይትናም ጠቅላይ ሚኒስትር ፋም ሚን ቺን በቤተ መንግስታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ደማቅ አቀባበል በማድረግ መወያየታቸውንም አንስተዋል፡፡

በውይይታቸውም በተለይም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትስስር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አብራርተዋል፡፡

ቬይትናም በብዛት የምትታወቀው መዋዕለ ንዋይ በመሳብ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሀገሪቱ በኢኮኖሚ፣ ኢንዱስትሪ፣ ግብርና እና ሌሎች ዘርፎች ተሞክሮ መቀሰሙን ገልጸዋል፡፡

ከሀገሪቱ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በተደረጉ ውይይቶች በኢትዮጵያ አሁን ላይ ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ግንኙነቱን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚፈልጉ መናገራቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በአፍሪካ በኢነርጂው ዘርፍ መዋእለ ነዋይ በማፍሰስ ኢንቨስትመንቶችን ማበረታታት እንደሚገባ ማንሳታቸውን ተናግረዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ በታዳሽ ሃይል ልማት በቀዳሚነት የምታደርገው ጥረትና በአህጉሪቱ ይኸው መንጸባረቅ እንዳለበት መግለጻቸውን ሀላፊዋ አንስተዋል።

ሀገር በቀል የሆኑ እንደ አረንጓዴ አሻራ ያሉ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን መግታት የሚያስችሉ ኢንሼቲቮች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ መጥቀሳቸውን አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ በምግብ ራስን ለመቻል በምታደርገው ግስጋሴ በጉብኝቱ ከቬይትናም ሰፊ ልምድ የቀሰመችበት፣ በግብርና በኢንዱስትሪ እና በሌሎች ዘርፎችም በርካታ ተሞክሮ የወሰደችበት እንደነበረም መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በተጨማሪም የቬይትናም ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ባሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እንዲሳተፉ የሚያስችል የሁለትዮች ምክክር የተደረገበት ነውም ብለዋል።

May be an image of 1 person, eyeglasses and newsroom

All reactions:

6060

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review