የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ በጃን ሜዳ የታቦታት ማደሪያ የጽዳት መርሐግብር ተካሄደ

You are currently viewing የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ በጃን ሜዳ የታቦታት ማደሪያ የጽዳት መርሐግብር ተካሄደ

AMN – ጥር 9/2017 ዓ.ም

“የጥምቀት በዓልን በጽዱ አዲስ አበባ! ” በሚል መሪ ቃል የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ በጃን ሜዳ የታቦታት ማደሪያ የጽዳት መርሐግብር ተካሄዷል፡፡

በመርሐግብሩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የጽዳት አምባሳደሮች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡

በመርሐግብሩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ከተማ አስተዳደሩ ለበዓሉ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠርና በስኬት እንዲከበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲሰሩ መቆየቱን አስታውሰዋል።

የአዲስ አበባ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጸሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ አንዳችን የአንዳችን በዓል ደስታችን መሆኑን እና አክብሮታችንን ለመግለጽ ተገኝተናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ወክለው የተገኙት አባ ወልደ ጊዮርጊስ ፣ ሀገራችን የምትታወቅበት ፍቅር አብሮነት፣ አንድነት ወንድማማችነት መቻቻል ለመግለፅ በፅዳት ዘመቻው የተገኙ የተለያዩ እምነት ተከታዮችንና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በቤተክርስቲያኗ ስም አመስግነዋል።

በአልማዝ ሙሉጌታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review