የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ቀንዲል እና የሰው ልጅ የፅናት ምልክት ለሆነው ለ129ኛ የዐድዋ ድል በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ – አደም ፋራህ

You are currently viewing የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ቀንዲል እና የሰው ልጅ የፅናት ምልክት ለሆነው ለ129ኛ የዐድዋ ድል በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ – አደም ፋራህ

AMN – የካቲት 22/2017 ዓ.ም

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የኢትዮጵያውያን የጀግንነትና ህብረ ብሔራዊ አንድነት ፋና ወጊ፣ የአፍሪካውያን የድል አድራጊነት ምሳሌ፣ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ቀንዲል እና የሰው ልጅ የፅናት ምልክት ለሆነው ለ129ኛ የዐድዋ ድል በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን ብለዋል፡፡

አደም ፋራህ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ የዐድዋ ድል ያስተማረንን የጋራ እሴቶች፣ መከባበር እና መተባበር ላይ በመመስረት፣ ጠንካራ፣ ሁለንተናዊ ሉዓላዊነቷ የተረጋገጠ እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ሁላችንም በአርበኝነት ስሜት በቁርጠኝነት እንትጋ ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review