የፀረ-ተዋህሲያን መድሃኒቶች በጀርሞች መለመድ እያደረሰ ያለውን አሉታዊ ተፅእኖ ለመቀነስ በትኩረት እየተሰራ ነው

You are currently viewing የፀረ-ተዋህሲያን መድሃኒቶች በጀርሞች መለመድ እያደረሰ ያለውን አሉታዊ ተፅእኖ ለመቀነስ በትኩረት እየተሰራ ነው

AMN- ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም

የፀረ-ተዋህሲያን መድሃኒቶች በጀርሞች መለመድ እያደረሰ ያለውን አሉታዊ ተፅእኖ ለመቀነስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ገለፀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የፀረ-ተዋህሲያን መድሃኒቶች በጀርሞች መለመድን ለመከላከል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተዉጣጡ አማካሪ ኮሚቴ አዋቅሮ እየሰራ ሲሆን ተግባሩን ለማጠናክር ዉይይት እና የስራ አፈፃፀም ግምገማ ተካሂዷል።

የፀረ-ተዋህሲያን መድሃኒቶች በጀርሞች መለመድ በሰው፣ በእንስሳትና በአካባቢ እንዲሁም በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ የሚገኝ ዓለም አቀፍ ችግር መሆኑንም ነዉ ቢሮው ያመላከተው።

የፀረ ተህዋስያን መድሀኒቶች በጀርሞች መለመድ በኣለም አቀፍ ደረጃ በዓመት 1.27 ሚሊዮን ህዝብ ህይወት እንደሚያሳጣ እና በታዳጊ ሀገራት ችግሩ የከፋ እንደሆነ ጥናቶች እንደሚያሳዩ ተመላክቷል።

በቢሮው የመድሃኒት አቅርቦትና ስርጭት አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ተስፋ ታየ እንደተናገሩት አግባብ ያልሆነ የፀረ ተህዋስያን መድሀኒቶች አጠቃቀም መድሀኒቶች በበሽታ አምጭ ተህዋስያን በቀላሉ እንዲለመዱ የሚያደርጋቸዉ መሆኑን ገልጸዋል።

የፀረ ተህዋስያን መድሀኒቶች በጀርሞች መለመድ ዋነኛ ምክንያቶች መካከል መድሀኒቶችን ያለጤና ባለሙያ ትእዛዝ ገዝቶ መጠቀም ፣ በሃኪም የታዘዙ መድሀኒቶችን በታዘዘው አግባብ ሳይጨርሱ ማቋረጥ፣ መድሀኒቶችን በመቀነስ ወይም በመጨመር መዉሰድ እንደሆነም አንስተዋል፡፡

ህብረተሰቡ በሃኪም የሚታዘዙ መድሃኒቶችን በአግባቡ በመጠቀም ችግሩን መከላከል እንዳለበት ማሳሰባቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review