የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለትንሳኤ የእንኳን አደረሳሁ መልዕክት አስተላለፈ

You are currently viewing የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለትንሳኤ የእንኳን አደረሳሁ መልዕክት አስተላለፈ

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሐነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ!

የትንሳኤ በዓል እየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጅ በዘር ከአዳም የወረሰውን የሐጥያት እዳ ለመሰረዝ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት በዓል እንደሆነ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በጽኑ ይታመናል፡፡

ትንሣኤ ውድቀትን፣ መሸነፍን፣ ተስፋ ማጣትንና ባርነትን ሁሉ ድል የማድረግ ተምሳሌት ነው፡፡ ምክንያቱም ትንሳኤ ሞትን አሸንፎ መነሳት፣ እንደገና መቆም ማለት ነው!

የክርስትና እምነት ተከታዮች ባለፉት ሁለት ወራት በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ በቸርነት፣ በመተዛዘን እንደቆዩ ሁሉ በዓሉን ሲያከብሩም የደከሙትን በመደገፍ፣ ለአጡት በመስጠት፣ ለተራቡት በማብላት፣ በፍቅር፣ በሰላም፣ በአንድነትና በበጎነት እንዲሆን ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

በድጋሚ መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንላችሁ!

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review