የፖፕ ፍራንሲስ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

You are currently viewing የፖፕ ፍራንሲስ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

AMN – ሚያዝያ 18/2017 ዓ.ም

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ ተፈጽሟል።

በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ የበርካታ ሀገራት መሪዎች እና የተለያዩ ሀገራት ንጉሶች መገኘታቸው ተመላክቷል፡፡

በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች እና ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የመጡ ሰዎች ታድመዋል፡፡

የፖፕ ፍራንሲስ አስከሬን ሮም በሚገኘው ሳንታ ማሪያ ማጆሬ ቤተ ክርስቲያን (ባዚሊካ) በክብር አርፏል።

ሊቀ ጳጳሱ ባደረባቸው ከፍተኛ የሳንባ ሕመም የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቆይተው በያዝነው ሳምንት ሰኞ በ88 ዓመታቸው በመኖሪያ ቤታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ይታወሳል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review