ዩክሬን የክሪሚያን ድልድይ በውሃ ውስጥ ፈንጂዎች መምታቷን አስታወቀች

You are currently viewing ዩክሬን የክሪሚያን ድልድይ በውሃ ውስጥ ፈንጂዎች መምታቷን አስታወቀች

AMN – ግንቦት 27/2017 ዓ. ም

የዩክሬን የደህንነት አገልግሎት ሩሲያን እና ዩክሬንን በክሪሚያ ባሕረ ገብ መሬት በኩል የሚያገናኘውን ድልድይ በውሃ ውስጥ ፈንጂዎች መምታቱን አስታውቋል።

የደህንነት አገልግሎቱ የድልድዩን ድጋፎች ከ 1 ሺህ 100 ቲኤንቲ ጋር ተመጣጣኝ በሆነ ፈንጂ በመምታት ጉዳት ማድረሱን ገልጧል።

በፍንዳታው የተጎዱ ሰዎች እንደሌሉና ድልድዩ በጊዜያዊነት ለትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ መደረጉን የሩስያ መገናኛ ብዙሀን አስታውቀዋል።

ሩሲያ በጥቃቱ ላይ እስካሁን ምንም መልስ አልሰጠችም።

የዩክሬን የደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ሌተናል ጄኔራል ቫሲል ማልዩክ የክሪሚያ ድልድይ ለሩስያ ወታደሮች አቅርቦት ባለው ስልታዊ ሚና ምክንያት ኢላማ መሆኑን ቀጥሏል ብለዋል።

ሌተናል ጄኔራሉ ጨምረውም ‘’በግዛታችን ላይ ምንም አይነት ህገ-ወጥ የሩስያ ተቋማት ቦታ የላቸውም” በማለት በዩክሬን በተያዙ ግዛቶች ውስጥ ያሉ የሩሲያ መሠረተ ልማቶችን ለማጥቃት ያላቸውን ቁርጠኝነት ማረጋገጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review