ያሉንን አቅሞች እየደመርን ታላቅ ሀገርን ለመገንባት ሚዲያ ትልቅ አቅም አለው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN – ታኀሣሥ 25/2017 ዓ.ም

በቅርቡ በይፋ ውህደት በፈጠሩት ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እና ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት በአሁኑ መጠሪያቸው ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጉብኝት ማካሄዳቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስታውቀዋል፡፡

ተቋሙ በዘመናዊ መሳሪያዎች እና በጥራት የተደገፉ ተግባራትን የሚከናውን መሆኑን ከዚህ ቀደም በሚያቀርባቸው ስራዎች ይታወቃል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬም ያየነው ይህንኑ ነው ብለዋል።

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የሁለት ጠንካራ ሚዲያ ድምር ውጤት በመሆኑ ወቅቱ የሚፈልገውን አቅምና ብቃት ተላብሶ ሀገርና ህዝብን የሚጠቅም ስራዎች መስራት ይገባዋል ሲሉም በማኅበራዊ ትስስር አስፍረዋል፡፡

በዛሬ የሚዲያ ተቋሙ ምልከታችን በቀጣይ ድጋፍ የሚያሻቸው ጉዳዮች እንዳሉ ተመልክተናል ነው ያሉት፡፡

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በቀጣይ ዜናና ወቅታዊ፣ የምርመራና ማህበረሰብ ተኮር ስራዎችን ከተገቢ መረጃዎች ጋር ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ስራዎችን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

በመንግስት በኩል ሚዲያው ለሚያከናውናቸው ስራዎች ሁለንተናዊ ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review