ይህ የጾም እና የጸሎት ወቅት ለሀገራችን ሰላም ፍቅር እድገት እና ብልጽግና የምንለምንበት ነው-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing ይህ የጾም እና የጸሎት ወቅት ለሀገራችን ሰላም ፍቅር እድገት እና ብልጽግና የምንለምንበት ነው-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN-መጋቢት 11/2017 ዓ.ም

ይህ የጾም እና የጸሎት ወቅት ለሀገራችን ሰላም ፍቅር እድገት እና ብልጽግና የምንለምንበት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።

1446ኛውን የረመዳን ጾም በማስመልከት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያዘጋጀው የአፍጥር መርሃ ግብር ከከተማዋ የተለያዩ ክፍሎች ከተወጣጡ የእስልምና እምነት ተከታዮች ከአቅመ ደካሞች ጋር ተካሂዷል።

የመርሃ ግብሩን ተሳታፊዎች እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የረመዳን ወር የእስልምና መርህ በሚያዘው መሰረት መረዳዳት እና መደጋገፍ አቅመ ደካሞችንም ማሰብ ይገባል።

የከተማ አስተዳደሩ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ በ24ቱም የምገባ ማዕከላት ሁል ግዜ ማታ ማታ አቅመ ደካማ እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ለተጋለጡ የእምነቱ ተከታዮች የአፍጥር መርሃ ግብር እያዘጋጀ መሆኑንም ከንቲባ አዳነች ተናግረዋል።

በሰብስቤ ባዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review