ዲኬቲ ኢትዮጵያ የ136 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ ከጤና ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ስምምነት ፈረመ

You are currently viewing ዲኬቲ ኢትዮጵያ የ136 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ ከጤና ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ስምምነት ፈረመ

AMN-መጋቢት 9/2017 ዓ.ም

ዲኬቲ ኢትዮጵያ ለስነ-ተዋልዶ ጤና ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ የ136 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ ከጤና ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ስምምነት ፈርሟል፡፡

መንግስት የእናቶች እና ህጻናትን ሞት ለመቀነስ በተሰሩ ስራዎች ብዙ ለውጥ ማምጣት መቻሉን የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱን የፈረሙት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ገልጸዋል፡፡

ለተገኘው ውጤት የስነ-ተዋልዶ ጤና እና የቤተሰብ ዕቅድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደነበረው ተናግዋል፡፡

የተደረገው ድጋፍ በቀጥታ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት መሳሪያዎችን፣ መድሃኒቶችን እና የባለሙያዎች ስልጠና ለመስጠት አገልግሎት ላይ እንደሚውል የተገለጸ ሲሆን፣ ድጋፉ መንግስት በ2030 የእናቶች እና ህጻናት ህልፈትን ለመቀነስ የያዘውን እቅድ በቀጥታ የሚደግፍ ይሆናል ብለዋል፡፡

የተገኘውን ድጋፍ የጤና ቢሮዎች በአግባቡ በመጠቀም የፕሮግራሙን ቀጣይነት እንዲያረጋግጡ ዶ/ር ደረጀ መልእክት ማስተላለፋቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review