ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ የደቡብ ደቡብን የጋራ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በተለያዩ ዘርፎች ላይ መስራት እንደሚገባ ገለጹ

You are currently viewing ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ የደቡብ ደቡብን የጋራ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በተለያዩ ዘርፎች ላይ መስራት እንደሚገባ ገለጹ

AMN- ሚያዝያ 22/2017 ዓ.ም

የደቡብ ደቡብን የጋራ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በአካባቢው የሚገኙ ሀገራትን በግብርና፣ በኢነርጂ ልማት፣ በቴክኖሎጂ፣ በአይሲቲ፣ ወታደራዊ እና ንግድ ግንኙነቶች ላይ መስራት ይገባል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

በሪዮ ዴ ጃኔይሮ ሲካሄድ የሰነበተው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ተጠናቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)፣ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ አካታች እና አሳታፊ በሆነ መንገድ የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ሚናን በማጠናከር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር ሙሉ እና ውጤታማ ትግበራን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

የደቡብ ደቡብን የጋራ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በአካባቢው የሚገኙ ሀገራትን በግብርና፣ በኢነርጂ ልማት፣ በቴክኖሎጂ፣ በአይሲቲ፣ ወታደራዊ፣ ንግድ፣ ግንኙነቶች ላይ መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ተፎካካሪ ፍላጎቶች በአንድነት እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚነሱ ጥያቄዎች በቁርጠኝነት መመራት እና መታረቅ እንዳለባቸውም መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review